ሰላም እንኳን ወደ ትላልቅ ቋንቋ ሞዴሎች (LLM) እንኳን ደኅና መጣችሁ!
ስሜ ጆን ኢዌልድ ይባላል፣ የ Google Cloud የሥልጠና ባለሙያ ነኝ።
በዚህ ኮርስ ላይ የትላልቅ ቋንቋ ሞዴሎች ወይም ኤልኤልኤሞች (LLMs) ምንነት መግለጽ፣ የ LLM አጠቃቀምን በተግባር ማብራራት፣ ለሰው ሠራሽ አስተውሎት ጥያቄ አቀራረብን (ፕሮምት ቲዩኒግ) ምንነት ማብራራት፣ የ Google ን ጄነረቲቭ ኤአይ (ሰው ሠራሽ አስተውሎት) መሥሪያ መሣሪያዎችን እንዴት መጠቀም እንደምትችሉ ትማራላችሁ።
ትላልቅ ቋንቋ ሞዴሎች (LLMs) የጥቅል ትምህርት (Deep Learning) ንዑስ ክፍሎች ናቸው።
ስለ የጥቅል ትምህርት (Deep Learning) የበለጠ ለማወቅ ከፈለጋችሁ የኛን የጄነረቲቭ ኤአይ (Introduction to Generative AI) ኮርስ መግቢያ ትምህርት ቪዲዮ ተመልከቱ።
ኤልኤልኤሞች (LLMs) እና ጄነረቲቭ ኤይአይ ሁለቱም በጥቅል ትምህርት (Deep Learning) ሥር ያሉ ክፍሎች ሆነው አንዳቸው ከሌላኛው ጋር የተቆራኙ ናቸው።
ሌላው ስለ ሰው ሠራሽ አስተውሎት (ኤአይ) ብዙ ልትሰሙ የምትችሉበት መስክ ጄነረቲቭ ኤአይ ነው። ይህ የሰው ሠራሽ አስተውሎት አንዱ ዓይነት ሆኖ ጽሑፍን፣ ምስሎችን፣ ድምፅን እና ሲንተቲክ ዴታ መፍጠር የሚችል ነው።
እንግዲያው እነዚህ ትላልቅ የቋንቋ ሞዴሎች የሚባሉት ምንድን ናቸው?
ትላልቅ፣ መጠነ ሰፊ ዓላማ ያላቸው የቋንቋ ሞዴሎች አስቀድመው እንዲሠለጥኑ ሊደረጉና ለተወሰኑ ልዩ ዓላማዎች እንዲቃኙ ሊደረጉ የሚችሉ ናቸው።
አስቀድመው እንዲሠለጥኑ ሊደረጉና ለተወሰኑ ልዩ ዓላማዎች ሊቃኙ የሚችሉ ናቸው ስንል ምን ማለታችን ነው?
ውሻን ስታለምዱ ምን ኣንደምታደርጉ በዓይነ ሕሊናችሁ ሣሉ።
ብዙውን ጊዜ ውሻችሁን የምታለምዱት ቁጭ በል፣ ና፣ ተኛ፣ እረፍ ወዘተ የመሳሰሉ መሠረታዊ ትዕዛዞችን በመስጠት ነው።
እነዚህ ትዕዛዞች ውሻው በዕለት ተዕለት ሕይወቱ ከናንተ ጋር ተግባብቶ መኖር እንዲችል ከተፈለገ በቂ ናቸው። እነዚህን በትክክል ማድረግ የሚችል ውሻ እንደ ጎበዝ ውሻ ይቆጠራል።
ይሁንና እንደ ፖሊስ ውሻ፣ የአካል ጉዳት ላለባቸው ድጋፍ የሚሰጥ ወይም የአደን ውሻ የመሰለ ልዩ አገልግሎት መስጠት የሚችል ውሻን ማልመድ ከፈለጋችሁ ግን ተጨማሪ ትምህርት ለውሻው መስጠት ይኖርባችኋል።
ትላልቅ የቋንቋ ሞዴሎች የሚባሉትም እንግዲህ በዚሁ መንገድ እንዲሠለጥኑ የሚደረጉ አርቴፊሻል አስተውሎቶች ናቸው።
ትላልቅ የቋንቋ ሞዴሎች የተለመዱ ዓይነት የቋንቋ ፕሮብሌሞችን መልስ መስጠት እንዲችሉ ለአብነት በተለያዩ ኢንዱስትሪዎች ውስጥ ጽሑፍን በዓይነት በዓይነቱ ለይተው እንዲመድቡ፣ ለጥያቄ መልስ እንዲሰጡ፣ የሰነድን አጠቃሎ እንዲጽፉ፣ ብሎም አዲስ ወጥ መጣጥፍ ጽፈው እንዲያወጡ ተደርገው የሠለጠኑ ናቸው።
ከዚህ በተጨማሪ ሞዴሎች እንደገና ወደ ተወሰኑ የኢንዱስትሪው የተወሰኑ ክፍሎች ለምሳሌ በችርቻሮ (ቀጥታ ሽያጭ)፣ በፋይናንስ፣ እና በመዝናኛ ላይ ለዚሁ ልዩ ንዑስ የመረጃ ስብስብ (ዳታሴት) ተብሎ በተዘጋጀ አነስተኛ መጠን ያለው መረጃ ላይ ተመርኩዘው እንዲሠለጥኑ ሊደረጉና ለልዩ ዓላማ ጥቅም ላይ እንዲውሉ ማድረግ ይችላል።
በመቀጠል ፅንሰ ሐሳቡን እንደገና ወደ ሦስት የትላልቅ ቋንቋ ሞዴሎች ዋንኛ ባሕሪያት ከፋፍለን እንመልከተው።
ትላልቅ ስንል ሁለት ትርጒሞችን በውስጡ የያዘ ነው፦
- የመጀመሪያው በውስጡ ያለው እጅግ መጠነ ሰፊ የሆነ የሥልጠና መረጃ ስብስብ (ዴታሴት) ነው፤ አንዳንድ ጊዜ የመረጃው መጠን እስከ ፔታባይት ደረጃ ሊደርስ ይችላል።
- ሁለተኛው ደግሞ መለኪያ መስፈርቶቹን (ፓራሜትሮች) ብዛት ይመለከታል።
በኤምኤል (ማሽን ለርኒንግ) ውስጥ መለኪያ መስፈርቶች ብዙውን ጊዜ ሃይፐር-ፓራሜቶች በመባል ይጠራሉ። እነዚህ ፓራሜትሮች ጠቅለል ባለ አነጋገር ማኅደረ ትውስታዎች (ሜሞሪዎች) እና ማሽኑ ከሞዴል ሥልጠናው የሚማረው ዕውቀት ናቸው።
ፓራሜትሮች ሞዴሉ ለምሳሌ አንድ ጽሑፍ ምን ሊሆን እንደሚችል አስቀድሞ መገመት የሚችልበትን የፕሮብሌም ሶልቪንግ ችሎታ የሚገልጹ ክኅሎቶች ናቸው።
አጠቃላይ ዓላማው ስንል ሞዴሎቹ የተለመዱ ፕሮብሌሞችን ምላሽ ለመስጠት በቂ አቅም ማለት ነው። ሁለት ምክንያቶች ወደዚህ ሐሳብ እንድናመራ ያደርጉናል።
- የመጀመሪያው የሚከናወነው ድርጊት ምንም ይሁን ምን ለዚህ ከሚያስፈልገው ቋንቋ ዓይን ሲታይ በሰው ልጆች ቋንቋዎች መካከል ያለው ተመሳሳይነት ነው
- ሁለተኛው ደግሞ የግብዓቶች (አስፈላጊ ነገሮች) ውስንነት ነው።
የተወሰኑ ጥቂት ድርጅቶች ብቻ እንዲህ ያሉትን ትላልቅ የቋንቋ ሞዴሎች እጅግ መጠነ ሰፊ የሆነ የመረጃ ስብስብ (ዴታሴት) እና እጅግ በጣም ብዙ ፕራሜትሮችን ተጠቅመው ለማሠልጠን አቅሙ አላቸው።
እነዚህ ድርጅቶች ታዲያ ሌሎች ሊጠቀሙባቸው የሚችሉትን መሠረታዊ የቋንቋ ሞዴሎችን ቢፈጥሩስ ምን አለበት?
ይህ ጥያቄ ወደ መጨረሻው ነጥብ እንድናመራ ያደርገናል፦ አስቀድመው እንዲሠለጥኑ ሊደረጉና ለተወሰኑ ልዩ ዓላማዎች ሊቃኙ የሚችሉ የቋንቋ ሞዴሎች።
አስቀድመው እንዲሠለጥኑ ሊደረጉና ለተወሰኑ ልዩ ዓላማዎች ሊቃኙ የሚችሉ የቋንቋ ሞዴሎች ስንል ከመጠነ ሰፊ የመረጃ ስብስብ (ዴታሴት) ተነሥቶ እንደገና ወደ ውስን ወይም አነሰተኛ የመረጃ ስብስብ (ዴታሴት) እንዲጠብ ተደርጎ አንድ ልዩ ዓላማ እንዲያገለግል ለአጠቃላይ ዓላማ የሠለጠነ የቋንቋ ሞዴልን ማዘጋጀት ወይም ማሠልጠን ማለት ነው።
ትላልቅ የቋንቋ ሞዴሎችን ከመጠቀም የሚገኙት ጥቅሞች ግልጽና ቀጥተኛ ናቸው።
በመጀመሪያ አንዱ ነጠላ ሞዴል ብቻ ለተለያዩ ተግባራት ጥቅም ላይ እንዲውል ማድረግ ይችላል።
እንዲህ ብለን ስንናገር ከዚህ ቀደም ይቻላሉ ተብለው የማይታመኑ ነገሮችን አሁን ማድረግ እንችላለን እንደማለት ነው።
እነዚህ ፔታባይት መጠን ካለው ትልቅ የመረጃ ቋት (ዴታሴት) በተገኘ መረጃ ሠልጥነው በቢሊዮኖች የሚቆጠሩ መለኪያ መስፈርቶችን (ፓራሜትሮችን) ማመንጨት የሚችሉ ትላልቅ የቋንቋ ሞዴሎች የተለያዩ ተግባራትን ለማከናወን የሚያስፈልጋቸው አስፈላጊው ብልሃት (የአእምሮ ብስለት) አላቸው። እነዚህ ተግባራት ከአንድ ቋንቋ ወደ ሌላ መተርጐም፣ ያልተጠናቀቀ ዓርፍተ ነገርን በራሳቸው መሙላት፣ ጽሑፍን በዓይነት በዓይነቱ ለይቶ ማስቀመጥ፣ ለጥያቄ መልስ መስጠት እና ተጨማሪ ተግባራትን ያካትታሉ።
ሁለተኛው የትላልቅ የቋንቋ ሞዴሎች ጠቀሜታ በሚፈልጉበት መስክ የራስዎን ልዩ ፕሮብሌም ምላሽ ለመስጠት እንዲችሉ የሚፈልጉት ሥልጠና መጠን ዝቅተኛ መሆኑ ነው።
ትላልቅ የቋንቋ ሞዴሎች በመስኩ ትንሽ ሥልጠና (መረጃ ስብስብ / ትሬኒንግ ዴታ) ይዘው እንኳ አጥጋቢ ውጤትን ሊያስገኙ ይችላሉ።
በሌላ አነጋገር በትንሽ ወይም ያለ ምንም መነሻ መረጃ የሚጠበቅባቸውን ግዴታ (ተግባር) ለማከናወን ይችላሉ ማለት ነው።
አነስተኛ መነሻ መረጃ በመስጠት ሞዴሉን ማሠልጠን ትችላላችሁ። ያለ ምንም መነሻ መረጃ ሲባል ደግሞ ሞዴሉ በግልጽ በሚታይ ደረጃ ምንም ዓይነት ሥልጠና ሳይሰጠው የሚያከናውነው ተግባር ማለት ነው።
ሦስተኛው ጠቀሜታ የትላልቅ ቋንቋ ሞዴሎች አፈጻጸም ብቃት በየቀኑ ከሚያገኘው አዳዲስ መረጃና ፓራሜትሮች በመነሣት አሁንም በየቀኑ እያደገ በመሄድ ላይ ያለ መሆኑ ነው።
ለዚህ እንደ ምሳሌ እንዲያገለግለን “ፓልም” የተባለውን ሞዴል እንመልከት። ፓልም የሚለው ምህፃረ ቃል ሲተነተን Pathways Language Model ማለት ነው።
ፓልምን Google የለቀቀው እንደ ፈረንጆቹ አቆጣጠር ኤፕሪል 2022 ላይ ነበር። ፓልም በበርካታ ቋንቋዎች ያለ ምንም ችግር የተለያዩ በርካታ ሥራዎችን ማከናወን የሚችል በውስጡ 540 ቢሊዮን ፓራሜትሮችን የያዘ የቋንቋ ሞዴል ነው።
ፓልም ዴንስ ዲኮደር ኦንሊ ትራስፎርመር ሞዴል ነው።
540 ቢሊዮን መለኪያ መስፈርቶችን (ፓራሜትሮችን) በውስጡ የያዘ ነው።
ፓዝዌይ Google በተለያዩ በርካታ TPU U4 pods ላይ አንድ ነጠላ ሞዴልን ማሠልጠን የሚያስችለውን ፓዝዌይ ሲስተም ፈጥሮለታል።
ፓዝዌይ በአንድ ጊዜ በርካታ ሥራዎችን ማከናወን፣ በፍጥነት አዳዲስ ተግባራትን መማር የሚችል፣ እንዲሁም ዓለምን በተሻለ መረዳት መቻሉን ማሳየት የሚችል አዲስ የሰው ሠራሽ አስተውሎት (ኤአይ) ሞዴል ዓይነት ነው።
ይህ ሲስተም ፓልም የተበታተኑ የኮምፒውተር ቀመሮችን ለአሣላጮች መረጃውን በአንድ ቦታ ላይ ማግኘት የሚችሉበትን ምቹ ሁኔታ ይፈጥርላቸዋል።
ቀደም ሲል ፓልም ትራንፎርመር ሞዴል እንደሆነ ጠቅሰን ነበር።
ትራንስፎርመር ሲባል በሥሩ ኢንኮዲንግ ኮምፖነንት (ማመሣጠሪያ) እና ዲኮዲንግ (ምሥጢር መፍቻ) ኮምፖንነት በውስጡ የያዘ ነው።
የኢንኮደሩ ሥራ የግቤት (ገቢ መረጃን) በቅደም ተከተሉ ጠብቆ መቀበል ሲሆን መረጃውን ከተቀበለ በኋላ ወደ ዲኮደሩ ሲያስተላልፈው ዲኮደሩ ደግሞ ተዛማጅነት ያላቸውን መረጃዎች እንዴት ማውጣት እንዳለበት አስቀድሞ የሠለጠነ በመሆኑ የሚፈለገውን መረጃ እንዲወጣ ያደርጋል።
ከተለመደው ዓይነት ፕሮግራሚንግ ተነሥተን ዛሬ ላይ ወደ ኒውራል ኔትዎርክስ ብሎም ወደ ጄነረቲቭ ሞዴሎች እስከምንድረስ ድረስ ብዙ መንገድ ተጉዘናል።
በተለመደው ዓይነት ፕሮግራሚንግ አንድን ኮምፒውተር ድመትን ለምሳሌ ለይቶ ማወቅ እንዲችል እጅግ አድካሚ የኮዲንግ ሥራ መሥራት ነበረብን። ዓይነት፦ እንስሳ፣ እግሮች፦ አራት፣ ጆሮዎች፦ ሁለት፣ ጸጉር አለው፦ አዎ፣ የክር ጉንጉንና ሚንት ቅጠል (ካትኒፕ) ትወዳለች እያለን።
አሁን ግን በኒውራል ኔትዎርክ ለኔትዎርኩ የድመትና የውሻ ሥዕል ሰጥተነው ይሄ ድመት ነው ብለን ብንጠይቀው መሆን አለመሆኑን በራሱ መገመት ይችላል።
በጄነረቲቭ ዌቭ ደግሞ እኛ እንደ አንድ ተጠቃሚ የራሳችንን ይዘት በጽሑፍ፣ በምስል፣ በድምፅ፣ በቪዲዮ ወይም በሌላ መልኩ መፍጠር የምንችልበትን ዕድል እናገኛለን።
ለምሳሌ እንደ PaLM ወይም LaMDA ያሉ ሞዴሎች ወይም ለንግግር መተግበሪያዎች ጥቅም ላይ የሚውለው Language Model ከበይነ መረብ እጅግ፣ እጅግ በርካታ መረጃ በመውሰድ የቋንቋ ሞዴሎችን ያዘጋጃሉ። በመሆኑም በቀላሉ በጽሑፍ ወይም በንግግር ጥያቄ በመጠየቅ የምንፈልገውን መረጃ እናገኛለን።
ስለዚህ ድመትን ምንድን ነው ብላችሁ ስትጠይቁት፣ ስለ ድመት የተማረውን በሙሉ አንድ ላይ አሰባስቦ መረጃውን ይሰጣችኋል።
በመቀጠል የተለመደውን የማሽን ትምህርት (ኤምኤል) ከትላልቅ ቋንቋ ሞዴል ዝግጅት ጋር እያነጻጸርን እንመልከት።
የተለመደው የማሽን ትምህርት (ኤምኤል) ከትላልቅ ቋንቋ ሞዴል ዝግጅት ጋር ሲነጻጸር |
|
የተለመደው የማሽን ትምህርት ዝግጅት |
የትላልቅ ቋንቋ ሞዴል ዝግጅት (አስቀድሞ ከሠለጠኑ ኤፒአይዎች ጋር) |
· አዎ የኤምኤል ልዩ ክኅሎት ያስፈልጋል |
· ምንም የኤምኤል ልዩ ክኅሎት አያስፈልግም |
· የሥልጠና ናሙናዎች ያስፈልጋሉ |
· ምንም የሥልጠና ናሙናዎች አያስፈልጉም |
· አዎ ሞዴሉ መሠልጠን ያስፈልገዋል |
· ምንም ሞዴሉን ማሠልጠን አያስፈልግም |
· አዎ ማሰቢያ ጊዜ + |
· ስለ ፕሮምት ዲዛይን ያስባል |
· የሚጠፋ ጊዜን ለመቀነስ ይታሰባል |
|
ፕሮምት ዲዛይን ያስባል ሲባል ማድረግ የሚኖርባችሁ ነገር ግልጽ፣ እጥር ምጥን ያለ እና በቂ መረጃን የያዘ ጥያቄ ማዘጋጀት ብቻ ነው።
ይህ የመደበኛ ቋንቋ የሚሠራበት ሁኔታ ወሳኝ አንድ ክፍል ነው።
በመቀጠል በአንድ የትላልቅ ቋንቋ ሞዴል ነባራዊ አጠቃቀም ላይ የሚኖረውን ሁኔታ በጥያቄና መልስ ሂደት ባለው ገጽታ ተጠቅመን እንመልከት።
በተለምደው የቋንቋ ዝግጅት ሂደት ላይ ጥያቄና መልስ ምንድን ነው?
ጥያቄና መልስ (ኪውኤ) የተለመደ ቋንቋ ዝግጅት ሂደት ንዑስ መስክ ሆኖ በተለመደ ቋንቋ ለሚቀርቡ ጥያቄዎች በአውቶማቲክ መልስ የመስጠት ተግባር ነው።
የጥያቄና መልስ ሞዴሎች አንድ አስቀድሞ የተዘጋጀ ጽሑፍን በመጠቀም ለጥያቄው መልስ ማውጣት ይችላሉ። ይህ በአንድ ሰነድ ውስጥ መልስ ለመፈልግ ጠቃሚ የሆነ ሞዴል ነው። ጥቅም ላይ እንደሚውለው ሞዴል ዓይነት የሚወሰን ሆኖ መልሱ በቀጥታ አስቀድሞ ከተዘጋጀ ጽሑፍ ሊወጣ ወይም ከባዶ ተነሥቶ ሊዘጋጅ (ጄነሬት ሊደርግ) ይችላል።
የኪውኤ ሞዴሎች ሲስተም እጅግ መጠነ ሰፊ ከሆነ እና ኮድ የተዋቀረ ነው። በመሆኑም ለበርካታ ጥያቄዎች በተጨባጭ እውነታ ላይ የተመረኮዘ፣ ማብራሪያ የሚሰጥ፣ አስተያየትና ሐሳብን ያከለ መልስ ለመስጠት የሚያስችል አቅም አላቸው።
እዚህ ላይ ቁልፉ ነገር ጥያቄዎቹን በትክክል ለማቅረብ ስለ ጉዳዩ የተወሰነ ዕውቀት ሊኖራችሁ ይገባል።
ለምሳሌ የመስኩ ዕውቀት በአይቲ የተደገፈ የደንበኛ ድጋፍ አገልግሎት ለመስጠት፣ የጤና እንክብካቤ አገልግሎት ለመስጠት ወይም በመ/ቤት የግዢ ሰንሰለት ላይ አስፈላጊ ነው።
ጄነሬቲቭ ኪውኤ (ጥያቄና መልስ) ስንጠቀም ዓውዱ ላይ በመመርኮዝ ሞዴሉ ጽሑፍ በራሱ ነጻ ሆኖ ያመነጫል።
ጽሑፍ መጻፍ የሚችሉ ሞዴሎችን መጠቀም ስለሚችል በተፈለገው ጉዳይ ላይ ምንም ዕውቀት እንዲኖር አያስገድድም።
በመቀጠል ለ Bard የቀረቡ ሦስት ጥያቄዎችን እንመልከት። Bard የሚባለው ቻትቦት በ Google AI ተዘጋጅቶ የቀረበ ትልቅ የቋንቋ ሞዴል ነው።
ጥያቄ 1
የዚህ ዓመት ሽያጭ መቶ ሺሕ ዶላር ነው። ወጪ ደግሞ ስልሳ ሺሕ ዶላር ነው። የተጣራው ትርፍ ስንት ነው?
ይህ ጥያቄ ሲቀርብለት Bard ሒሳቡን እንዴት እንደሠራው አሳይቶ የተጣራውን ትርፍ ስንት እንደሆነ መልስ ይሰጠናል።
በመቀጠል Bard የተጣራ ትርፍ ስንል ምን ማለታችን እንደሆነ ማብራሪያውን አብሮ ይሰጠናል።
እነሆ ሌላ ሁለተኛ ጥያቄ ለ Bard
በመጋዘን ያለው ምርት ብዛት 6000 ነው። አዲስ የመጣው ትዕዛዝ ብዛቱ 8000 ነው። ምን ያክል ተጨማሪ ምርት ማዘጋጀት ያስፈልገኛል?
አሁንም Bard በመጀመሪያ የሒሳቡን ስሌት እየሠራ መልሱን ይሰጠናል።
የመጨረሻው ምሳሌያችን ደግሞ እንደሚከተለው ይመስላል።
በዐሥር ክልሎች ላይ 1000 ሴንሰሮች (አንፍናፊዎች) አሉን። በእያንዳንዱ ክልል ውስጥ በአማካይ ስንት አነፍናፊ (ሴንሰር) አለን?
Bard ፕሮብሌሙን እንዴት መልስ መስጠት እንደምንችልና ተጨማሪ ዓውዶችን ካሳየን በኋላ መልሱን ይሰጠናል።
ለእያንዳንዱ ጥያቄዎቻችን የሚፈለገው መልስ ለማግኘት ችለን ነበር።
ፕሮምት ዲዛይን ማለት ከቋንቋ ሞዴል የሚፈለገውን ምላሽ ለማግኘት ጥያቄ የምናቀርብበት ሂደት ነው።
ፕሮምት ዲዛይን እና ፕሮምት ኢንጂነሪንግ በተለመደ ቋንቋ ዝግጅት ላይ ያሉ በጣም ቅርርብ ያላቸው የተለያዩ ፅንሰ ሐሳቦች ናቸው።
ፕሮምቶችና ፕሮምት ኢንጂነሪንግ ምንድን ናቸው?
|
|
ፕሮምት ዲዛይን
|
ፕሮምት ኢንጂነሪንግ |
ፕሮሞቶች አንድ የሚፈለግ ተግባር እንዲያከናውን ለቋንቋ ሞዴሉ የሚሰጡ መመሪያዎችና ዓውዶች ናቸው። |
ፕሮምት ኢንጂነሪንግ የቋንቋ ሞዴልን ለተለያዩ ተግባሮች ለመጠቀም የሚቀርቡትን ፕሮሞቶች ወደ ላቀ ደረጃ የማድረስ እና የማዘጋጀት ተግባር ነው።
|
በርግጥ ሁለቱም ለቋንቋ ሞዴል ጥያቄ ማቅረብን የሚመለከቱ እንደ መሆናቸው ተመሳሳይነት አላቸው። ሆኖም ግን በሁለቱ መካከል ከላይ እንደሚታየው ቁልፍ ልዩነት አለ።
ለምሳሌ ሲስተሙ አንድን ጽሑፍ ከእንግሊዝኛ ወደ ፈረንሳይኛ እንዲተረጉም ከተጠየቀ፣ ጥያቄው (ፕሮምቱ) በእንግሊዝኛ መጻፍ አለበት፣ ትርጒሙ ወደ ፈረንሳይኛ መሆኑ በግልጽ ሊነገረው ይገባል።
በሌላ መልኩ ፕሮምት ኢንጂነሪንግ ሲስተሙ የተሻለ መልስ እንዲሰጥ አድርጎ የማመቻቸት ሂደትን ይመለከታል። ለዚህም በመስኩ ዕውቀት መኖርን፣ የተፈለገውን ውጤት ምን ሊመስል እንደሚገባ ምሳሌዎችን መስጠት፣ ወይም ለሲስተሙ በተለይ ይበልጥ ውጤታማ እንዲሆን ሊያደርጉት የሚችሉትን ቁልፍ ቃላት መርጦ መስጠትን ይመለከታል።
ፕሮምት ዲዛይን በግርድፉ ሲታይ ጠቀለል ያለ ፅንሰ ሐሳብ ሲሆን በአንጻሩ ፕሮምት ኢንጂነሪንግ በአንድ ጉዳይ ላይ ትኩረት የሚያደርግ ፅንሰ ሐሳብ ነው።
ፕሮምት ዲዛይን አስፈላጊ መሆኑ እንደተጠበቀ ሆኖ ፕሮምት ኢንጂነሪንግ የሚያስፈልገው ግን ከፍተኛ ትክክለኛነት ወይም የአፈጻጸም ብቃት በሚያስፈልግበት ሁኔታ ውስጥ ነው።
ሦስት ዓይነት የትላልቅ ቋንቋ ሞዴል ዓይነቶች አሉ፦ ጀነሪክ የቋንቋ ሞዴሎች፣ በመመሪያ የተቃኙ እና በንግግር የተቃኙ የቋንቋ ሞዴሎች ናቸው።
ሦስት ዓይነት ዋንኛ የኤልኤልኤም ዓይነቶች ያሉ ሲሆን እያንዳንዳቸው በተለያየ መንገድ ጥያቄ እንዲቀርብላቸው ያስፈልጋቸዋል።
የመጀመሪያዎቹ ሁለቱ በቀላሉ ሊምታቱብንና በጣም የተለያየ ውጤት ሊያስገኙልን ይችላሉ።
ጀነሪክ (ጥሬ) የቋንቋ ሞዴሎች፦ እነዚህ ሞዴሎች በሠለጠኑበት ውሂብ ጎታ (የመረጃ ቋት) ላይ በመመርኮዝ ቀጣዩ ቃል ምን ሊሆን እንደሚችል ይገምታሉ።
በመመሪያ የተቃኙ ሞዴሎች፦ በግቤት (በሚቀርብላቸው መረጃ) ላይ ባለው መመሪያ ተጠቅመው መልሱን እንዲገምቱ ተደርገው የሠለጠኑ ናቸው።
በንግግር የተቃኙ ሞዴሎች፦ ቀጣዩ ምላሽ ምን ሊሆን እንደሚችል በመገመት ንግግር (ምልልስ) ማድረግ እንዲችሉ ተደርገው የሠለጠኑ ናቸው።
የሚከተለው የጀነሪክ ቋንቋ ሞዴል ምሳሌ ነው።
የሚከተለው በመመሪያ የሠለጠነ ሞዴል ምሳሌ ነው።
በንግግር (በምልልስ) የሠለጠነ ሞዴል እንዴት እንደሚሠራ፦
ሞዴሎች ለመልሱ ምክንያቱን የሚያብራራ ጽሑፍ ከሰጡ በኋላ ትክክለኛውን መልስ በመስጠት ላይ የተሻሉ ናቸው።
ሞዴሉ በመጀመሪያ ሲጠየቅ ትክክለኛ መልስ የመስጠት ዕድሉ አናሳ ነው።
ከዚህ በታች እንደሚታየው በሦስተኛው ደረጃ ላይ የተሻለ መልስ ሲሰጥ ማየት ይችላል።
ትዝብት
ሁሉንም ማድረግ የሚችል ሞዴል የራሱ የሆኑ ተግባር ላይ የሚንጸባረቁ ውስንነቶች አሉት።
በተግባር ላይ የተወሰነ ቅኝት ኤልኤልኤሞችን የበለጠ አስተማማኝ እንዲሆኑ ያደርጋቸዋል።
Vertex AI በተግባር ላይ የተመረኮዙ ሞዴሎችን ይሰጠናል።
እስኪ በመቀጠል አጠቃቀም ላይ የተመረኮዘ ተግባር ሞዴሉ እንዲያከናውን ፈልጋችኋል እንበል። ለምሳሌ ደንበኞች ምን እንደሚሰማቸው ማወቅ ወይም በሌላ አባባል ደንበኞች በምርታችሁ ወይም በአገልግሎታችሁ ምን ዓይነት አመለካከት እንዳላቸው ለማወቅ ፈልጋችኋል እንበል።
የስሜት ትንታኔ መስጠትን ተግባር ማከናወን የሚችለውን ሞዴል መምረጥ ትችላላችሁ።
ሞዴሉን እንደምንፈልገው አድርገን መቃኘት
ሞዴሉን መቃኘት ማለት ሞዴሉን ወደ አንድ አዲስ መስክ ወይም ወደ ተለመዱ ዓይነት ውስን አጠቃቀሞች አዲስ መረጃ (ውሂብ) እየሰጡ የማለማመድ (የማሠልጠን) ሂደት ነው። ለምሳሌ፣ የሥልጠና መረጃ ሰብስበን ኤልኤልኤምን ለሕግ ነክ ሥራዎች ወይም ለሕክምና ሙያ በተለየ መልኩ እንዲዘጋጅ ማድረግ እንችላለን።
በተጨማሪ የመረጃ ቋታችሁን (ዳታሴት) በማምጣት ሞዴሉን በኤልኤልኤም ውስጥ እንደገና እየቃኛችሁ በድጋሚ ልታሠለጥኑት ትችላላችሁ። ይህ ከባድ የሥልጠና ሥራን መሥራትን ይጠይቃል። በዚህም የራሳችሁ የሆነ በደንብ የተዘጋጀ ሞዴል እንዲኖራችሁ ማድረግ ትችላላችሁ።
ከዚህ በታች የምታይት በሕክምና ሙያ የሠለጠነ ሞዴል ነው።
ተግባራቱ ጥያቄና መልስ፣ ምስል ትንታኔ፣ ተመሳሳይ ታካሚዎችን ማግኘት ወዘተ ያካትታሉ።
ይበልጥ ሞዴልን እንዲቃኝ ማድረግ ውድ ሊሆንና ብዙውን ጊዜ በቀላሉ ሊተገበር የማይችል ሊሆን ይችላል።
እና የተሻሉ መቃኛ ዘዴዎች አሉ? አዎ።
ብቃት ያለው ፕራሜትር ተጠቅሞ መቃኛ ዘዴዎች፦ ኤልኤልኤምን በራሳችሁ መረጃ ተጠቅማችሁ ሞዴሉን ማራባት ሳይኖርባችሁ መቃኘት የምትችሉባው ዘዴዎች ናቸው። ዋናው ሞዴል አይቀየርም። ከዚህ ይልቅ በላዩ ላይ ያሉ ተጨማሪ ትናንሽ ነገሮች እንዲቃኙ ይሆናሉ። እነዚህን በተፈለገ የተለያየ ጊዜ መበወዝና መቀያየር ይቻላል።
ፕሮምት ዝግጅትን መቃኘት፦ ጥሩ ከሆኑ የመቃኛ ዘዴዎች መካከል አንዱ ነው።
ጀኔረቲቭ ኤአይ ስትዲዩ በፍጥነት Google Cloud ላይ መተግበሪያችሁን በቀላሉና በፍጥነት እንድትቃኙ ያስችላችኋል
Generative AI App Builder ምንም ኮድ መጻፍ ሳያስፈልግ በራሳችሁ ጀነረቴቭ ኤአይ መተግበሪያዎችን መፍጠር እንድትችሉ ያደርጋችኋል። ለዚህም የሚሆኑ የተለያዩ መሣሪያዎችን ያቀርብላችኋል። ከሌሎች አልሚዎች ጋርም መወያየት፣ መነጋገር የምትችሉበትን መድረክም በውስጡ የያዘ ነው። በቀላሉ እየጎተታችሁ መተግበሪያዎችን ወደ ሞዴላችሁ ማስገባት፣ ጽሑፎችን፣ ምስሎችን ቪዲዮዎችን በቀላሉ መፍጠር እና አርትዕ ማድረግ የሚያስችላችሁን ቪዥዋል ኤዲተር እንዲሁም በቀላሉ ፍለጋ የምታደርጉበትን እና ንግግር (ምልልስ) ማድረግ የምትችሉባችውን መሣሪያዎችን እና ሌሎች ምቹ ሁኔታዎችን ያቀርብላችኋል።
የራሳችሁን ቻትቦት፣ ዲጂታል ረዳት፣ ብጁ የፍለጋ ኢንጂኖች፣ የዕውቀት ማከማቻ ቦታ፣ የሥልጠና መስጫ መተግበሪያዎች፣ እና ሌሎች ነገሮችን በራሳችሁ መፍጠር እንድትችሉ ያደርጋችኋል።
PaLM API: ወደ Google LLMs በቀላሉ የሚያስገባ ነው። መተግበሪያ አልሚው እንደ አጠቃሎ ሰጪ፣ ምደባ ሠሪ እና ተጨማሪ ነገሮች የሚያደርጉ ሞዴሎች መድረስ የሚችልበትን መንገድ ያመቻችታል።
MakerSuite: ፕሮቶታይፖችን መሥራት ለመጀመር ቀላል የሆነ መንገድ ሲሆን ጄነረቲቭ ኤአይ መተግበሪያዎችን ለመገንባት ያስችላል። በፕሮምቶች፣ በመረጃ ቋታችሁ (ዳታሴት) ላይ በመመርኮዝ ሲንተቲክ መረጃ በማዘጋጀት ሞዴሉን በተፈለገው መንገድ እንድታቃኙ ያደርጋችኋል።
ለበለጠ ውጤት አልሚዎች ሁለቱንም PaLM API እና MakerSuite አንድ ላይ በማቀናጀት መጠቀም ይችላሉ።
ይህን ማድረግ የሚያስችላቸው የ Google ስዉት በውስጡ ሞዴል ማሠልጠኛ መሣሪያን፣ ሞዴል ሥራ ማስጀመሪያ መሣሪያ፣ እና ሞዴል መቆጣጠሪያ መሣሪያን የያዘ ነው።
ለዛሬ ይኸው ነው፣ እናመሰግናለን።